በአፋር ከ200 በላይ ንጹሀን መጨፍጨፋቸው ዩኒሴፍን አሳስቦታል
👉የሰብአዊ የተኩስ አቁም ተግባራዊ እንዲሆንም ጠይቋል፤
አሸባሪው ህወሓት ይህንን የተናጠል የተኩስ አቁም ጎን በማለት ህጻናትን ጭምር በማስታጠቅ የአፋር እና የአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ህጻናትን ጨምሮ 240 ሰዎችን መጨፍጨፉን ተከትሎ ዩኒሴፍ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የኒሴፍ የሰብአዊ የተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ሲልም ጠይቋል።
በጤና ጣቢያ ውስጥ ተጠልለው በነበሩ ንጹሀን ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ200 በላይ የሚሆኑት መጨፍጨፋቸውን የገለጸው ዩኒሴፍ፤ ከእነዚህም መከላል ከ100 በላይ የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን አስታውቋል።
በቀጠለው የቡድኑ ትንኮሳ ምክንያት በክልሎቹ ላይ በተለይም ህጻናት ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ መሆኑን በርካቶችም እየተፈናቀሉ እንደሆነ ዩኒሴፍ በመግለጫው ጠቅሷል።
ይህ ሰብአዊ ቀውስ እንዲያበቃ የሰብአዊ ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ያለው ዩኒሴፍ፤ ለንጹሀን ጥበቃ እነዲደረግም አሳስቧል።
መንግስት የሰብአዊ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አሳልፎ ከትግራይ ክልል መውጣቱ ይታወቃል። ይሁን እነጂ አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን ወደ አማራና እና አፋር ክለሎች በማስፋት ንጹሀንን እየጨፈጨፈ ይገኛል።