You are currently viewing አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 220 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 220 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

  • Post comments:0 Comments
አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች 220 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው እንዳሉትም የተመድ የእርዳታ እና የሰብዓዊ መብት ኀላፊ ማርቲን ግሪፍቲ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከተቋማት ኀላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል።
አቶ ደመቀ ከዚህ በፊት ተቋሙ ላደረገው እርዳታ በማመስገን ስለተናጠል ተኩስ አቁሙ እና ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ማድረስ ያልተቻለበትን ምክንያት አስረድተዋቸዋል ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ በከፈተው ጦርነት 220 ሺህ ሰዎች ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች መፈናቀላቸውን አቶ ደመቀ ያብራሩላቸው ሲሆን ይህን ተቋማቸው አለማውገዙ ትክክል አለመሆኑን አስረድተዋቸዋል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።
ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይደርስ ያደረገው አሸባሪው ቡድን መሆኑን በመግለጽ በዚህ ወቅትም በአፋር ክልል ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደቦታው ሄደዋል ብለዋል።
ማርቲን ግሪፍቲ በበኩላቸው አሸባሪው ትህነግ እያደረገ ያለው አንቅስቃሴ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ለኢትዮጵያ የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ አቋማቸውን አሳውቀዋል ብለዋል አምባሳደር ዲና።
አቶ ደመቀ በበይነ መረብ ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መምከራቸውም ተብራርቷል።

ምላሽ ይስጡ