በአገራችን ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን … የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች
በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀልበስ በግዳጅ ላይ ላለው ለአገር መከላከያ ሰራዊትእና ለጸጥታ ሃይል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ ኃይል ደም ለግሰዋል፡፡
ሰራተኞቹ በዚሁ ወቅት በኢትዮጵታ ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀልበስ በግዳጅ ላይ ላለው ለአገር መከላከያ ሰራዊት እና ለጸጥታ ሃይል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።