You are currently viewing “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በሀረሪ ክልል የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ

“ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በሀረሪ ክልል የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
“ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በሀረሪ ክልል የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ
“ደማችን ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል ለሀገር ደጀን ለሆነው የመከላከያ ሠራዊትና ከየክልሉ የህልውና ዘመቻ ተሳታፊ የፀጥታ ሀይሎች የደም ልገሳ መርሐ ግብር የሀረሪ ክልል ም/ርእሰ መስተዳደር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሀረር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።
በደም ልገሳ መርሃግብሩ ላይ ተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንዳሉት የክልሉ ህዝብ ከዚህ ቀደም በህግ ማስከበር ዘመቻም የደም ልገሳ እና ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ማህበረሰቡ በስንቅ ዝግጅት፣ ገንዘብ በማሰባሰብ፣ በደም ልገሳ እና በሌሎች ድጋፍ ስራዎች አለኝታነቱን በቁርጠኝነት እያሳየ ይገኛል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በክልሉ በሚዘጋጁ የተለያዩ መድረኮች ሰራዊቱን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነቱንም እየገለፀ ይገኛል ሲሉ አመላክተዋል፡፡
የደም ልገሳ ፕሮግራሙ በዋናነት የሚካሄደው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ከየክልሉ ለህልውና ዘመቻ የተሰማሩ የፀጥታ ሀይሎች ድጋፍ ለማሳየት የሚችል መሆኑን የሀረሪ ክልልብብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ተናግረዋል ፡፡
ጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊታችን የጁንታውን ህወሃት ቡድንን ለመደምሰስና የሀገራችን ህልውና ለማስጠበቅ በሚያደርገው የህልውና ዘመቻ በሁሉም መልኩ ለመደገፍ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ለማሳየት የደም ልገሳው እየተካሄደ እንደሆነም አቶ አብዱጀባር ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡም ሆነ ወጣቱ ደም ከመለገስ ጎን ለጎን የሀብት ማሰባሰብ እና የመከላከያ ምልመላዉንም ትኩረት በመስጠት ከምንም በላይ መቅደም ያለበት እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
በክልሉ እየተከናወነ ባለው የደም ልገሳ መርሀግብር ከ500 ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ምላሽ ይስጡ