You are currently viewing የመዲናዋ ወጣቶች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

የመዲናዋ ወጣቶች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

  • Post comments:0 Comments
የመዲናዋ ወጣቶች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንደሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ለቀረበላቸው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “ውድ የኢትዮጵያ መዲና የአዲስ አበባ ወጣቶች እስካሁን ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊታቻንን ለመቀላቀል የተመዘገባችሁና ገና ያልተመዘገባችሁ ፍጠኑ ከወንድሞቻችሁና ከእህቶቻችሁ ጋር ተሰለፉ” ሲሉ ጠይቀዋል።
በመላ ሀገሪቱ ወጣቶች በትናንትናው ዕለት በሀገር ላይ የታወጀውን ሴራ ለመመከት ለቀረበላቸው ጥሪ የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑንም አውስተዋል።
“የጀግኖች አባቶቻችን የሀገር ፍቅር፣ የጀግንነት እና የአይበገሬነት ወኔ ዳግም በዚህ ትውልድ ይደምቃል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ የህወሓት ጁንታን አርቀን በመቅበር በሀገር ላይ የተከፈተውን የውክልና ጦርነት በድል እናጠናቅቀዋለን” ብለዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ