You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…

  • Post comments:0 Comments

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ያላትን አካባቢያዊም ሆነ አህጉራዊ አቅም እንደሚያጠናክርና ብሔራዊ ክብሯን እንደሚያስጠብቅ አጥብቀን ስለምንረዳ በአሁኑ ሰዓት ቀዳሚ ሀገራዊ አጀንዳችን አድርገን ይዘነዋል።

ግድቡ ለዜጎች ብሔራዊ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ይታወቃል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ኢትዮጵያዊያን ከድህነት ለመውጣት የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ትግል እውን ማድረጊያ ፕሮጀክት መሆኑን በውል ተረድተውት ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

ሀይል ከማመንጨት ባሻገር የመተባበር፣የአንድነት፣እርስ በእርስ ያለንን ግንኙነት ያጠናከረ፣ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያለንን ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችንን የበለጠ የሚያጎለብት እንዲሁም የይቻላል መንፈስን ያሣዬን ጭምር በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊያን በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ በከፍተኛ ርብርብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ምላሽ ይስጡ