የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የላቀ ሚና ለተጫወቱ አካላት ምስጋና አቀረቡ

  • Post comments:0 Comments
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የላቀ ሚና ለተጫወቱ አካላት ምስጋና አቀረቡ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠላቶች ከውስጥም ከውጭም የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ እየሰሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ እንድታካሂድ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ፣ ኢትዮጵያ እንታሸንፍ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታ አካላት እና የሚዲያ ተቋማት የነበራቸውን ገንቢ ሚና አድንቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገራዊ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲናቀቅ ለሰጡት በሳል አመራርም የምክር ቤቱ አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮች የታረሙበት እና ህዝብ ብርድና ዝናብ ሰይበግረው በነቂስ ወጥቶ የተሳተፈበት መሆኑን በማንሳት የእንኳን ደስ አለን መልእክት አስተላለፈዋል፡፡
ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ ከመጠናቀቁም በላይ መራጮች በየምርጫ ክልላቸው ችግኞችን በመትከል አረጓጓዴ ዐሻራቸውን ያሳረፉበት መሆኑንም የምክር ቤቱ አባላት በአዎንታዊነት አንስተዋል፡፡
“ኢትዮጵያውያን በህዝች ተሳትፎ የተሳካ ሰላማዊ ምርጫ በማሄዳችን አንኳ ደስ አለን” ያሉት የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሀገሪቱን ብልፅግና ለማረጋጥ የያዟችው ውጥኖች እንዲሳኩ ፈጣሪ እንዲረዳቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ