You are currently viewing የኢትዮጵያ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድምጽ ሰጪዎች በተሳተፉበትና በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ ነው- የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን

የኢትዮጵያ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድምጽ ሰጪዎች በተሳተፉበትና በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ ነው- የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን

  • Post comments:0 Comments

የኢትዮጵያ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድምጽ ሰጪዎች በተሳተፉበትና በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ ነው- የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን
*****************************

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድምጽ ሰጪዎች የተሳተፉበት መሆኑንና ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል፡፡

የታዛቢ ቡድኑ 96 የምርጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ በጎበኛቸው የምርጫ ጣቢያዎች በርካታ የሕግ አስከባሪ አካላት መኖራቸውን፣ እንዲሁም በምርጫ ጣቢያዎቹ ለአካል ጉዳተኞችና ለአዛውንቶች ቅድሚያ እንደተሰጠ መታዘቡን አስታውቋል፡፡

መራጮች ሚስጥራቸው በተጠበቀ መልኩ ድምጽ እየሰጡ መሆናቸውንም ታዛቢ ቡድኑ አስታወቋል፡፡

የታዛቢ ቡድኑ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው እንደተከፈቱ መታዘቡን ገልጿል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን መራጮች በምርጫ ቀንና የምርጫ ውጤት ከተገለጸ በኋላ የምርጫውን ሰላማዊነት እንዲያስጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሕግ አስከባሪ አካላትም የሙያ ግዴታቸውን ሲወጡ በሰላማዊ መንገድ እንዲሆን ታዛቢ ቡድኑ ጠይቋል፡፡

ምላሽ ይስጡ