ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የለውጥ ጉዞውን ዳር ለማደረስ ይሰራል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የለውጥ ጉዞውን ዳር ለማደረስ ይሰራል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የለውጥ ጉዞውን ዳር ለማደረስ ይሰራል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
የብልጽግና ፓርቲ የህዝቦችን አንድነትና ወንድማችነት በማጠናከር የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ እንደሚሰራ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባል አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ በጋምቤላ ክልል የመጨረሻውን የምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አካሄዷል።
በማጠቃለያ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደተናገሩት ፓርቲው የሚመራው መንግስት ባለፉት ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋትና ጉድለቶችም በማረም የህዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲሰራ ቆይቷል።
ብልጽግና በተለይም የውጪ ጣልቃ ገብነትንና የውስጥ ተባባሪዎቻቸውን በጋራ ክንድ በመመከት የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋ ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በትጋት እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑም ገልጸዋል።

Leave a Reply