ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅማ ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን እና ሌሎች ሚንስትሮች ጋር በመሆን ነው ወደጅማ ያቀኑት።
በቆይታቸውም በጅማ ከተማ በአዌቱ ወንዝ ላይ የተገነባውን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጅማ ስታዲየምም ተገኝተው ለከተማው እና አካባቢው ህዝብ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።