የሀገራችንን ጥቅምና የዜጎቻችንን…

የሀገራችንን ጥቅምና የዜጎቻችንን…

  • Post comments:0 Comments
የሀገራችንን ጥቅምና የዜጎቻችንን ክብር የሚያስጠብቅ የውጭ ግንኙነት ተቋማትን ለመገንባት ብልጽግናን ይምረጡ!
በእያንዳንዱ ሂደትም ሆነ በፖሊሲያችን እንዲሁም በእየለቱ እየተጠናከሩ በመጡ ተቋሞቻችን የምናንፀባርቀው ቀዳሚ ጉዳይ ሀገራዊ ክብራችን ነው፡፡የዜጎችን ክብር ከማስጠበቅ አንጻር፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለ ሰላማዊ ግንኙነትን በማስቀጠል እና ጠንካራ የውጭ ግንኙነት አስፈጻሚ ተቋማት በመገንባታ ረገድ በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት ዘርፍ ነው።
በለውጡ ማግስት ብልጽግና ፓርቲ በርካታ ለውጦችንና የሪፎርም ርምጃዎችን በዘርፉ ላይ ያከናወነ ሲሆን፤ በውጭ ግንኙነት ዘርፉ የነበሩ የዕይታ ጉድለቶችን፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችንና የተልዕኮ ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።
ከዚህም ባሻገር ቀዳሚው የውጭ ግንኙነታችን ዓላማ የሆነውን የሀገር ሉዓላዊነት እና የዜጎች ደህንነትንና ክብርን የሚያስጠብቅ ብቁ ቁመና ያለው ጠንካራ የመከላከያ አቅምና የደህንነት ተቋማት ግንባታ ላይም አያሌ ለውጦች አስመዝግበናል።
ብልፅግና የኢኮኖሚ ፍላጎት መሟላት ብቻ አይደለም፡፡ የዜጎችና የሀገር ክብርን ይጨምራል፡፡በመሆኑም ፓርቲያችን የሚተገብረው የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ሁለቱንም መንትያ ግቦች የሚያሳካልን ይሆናል፡፡
በአንድ በኩል የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችልና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብር በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራዊ ክብርን የሚያስጠብቅ፣ የዜጎችን መብት፣ ክብርና ደህንነት የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ይህንን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማሳካት ግንኙነት የረጅም ጊዜ ሉዓላዊ ሀገርነትን፣ ነፃ የመንግስትነት ታሪክን፣ መቻቻል ያለበት ብዝሃነትን፣ መልካም መስተጋብሮች፣ መወራረሶችና አብሮነቶች ባለቤት ሀገር ውስጥ የፌዴራሊዝም ጅማሮዎች መኖርን እንደ እሴት የሚያገናዝብ ነው፡፡
ፓርቲያችን የሚከተለው የውጭ ግንኙነት ከሀገር ውስጥ ጉዳያችን ያልተነጠለ እና ሀገራዊ ሁኔታችንን መነሻ የሚያደርግ እንዲሁም የውጭውን ከባቢ የሚያገናዝብ ነው፡፡ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የሀገር ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅምን በጽኑ መሠረት ላይ መገንባት ነው ብለን እናምናለን።
ለሀገር ሉዓላዊነትና ለዜጎች ክብር ብልጽግናን ይምረጡ!

Leave a Reply