የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ…

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ…

  • Post comments:0 Comments

እሳቤ በኢትዮጵያ ዘላቂ እና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ነው

የብልፅግና ፓርቲ ገዢ ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን የዘንድሮውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ መርሆዎችን በተከተለ መንገድ እንዲካሄድ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት እና ለማዳበር የምርጫው ፍትሃዊነትና ተዓማኒነት ያለውን ወሳኝነት በሚገባ በመገንዘብ ከተወዳዳሪነት ባሻገር በርካታ ተግባራትን በከፍተኛ ኃላፊነት እያከናወነ ይገኛል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ እሳቤ በኢትዮጵያ ዘላቂ እና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በሀገሪቱ ለሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች አርዓያ የመሆን ኃላፊነት እንዳለበት በማመን ለህዝቡ በግልፅ የሚታዩ ተግባራትን  እያከናወነ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሎሎች ባለድርሻ አካላት በሀገራችን አስተማማኝ የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ ምርጫው ያለውን ሀገራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች በሚገባ ተረድተው አርአያ በመሆን መላውን ህዝብ ለምርጫው ስኬታማነት የበኩሉን በጎ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ትክክለኛውን አቅጣጫ እንዲከተል ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

Leave a Reply