ምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

ምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
ምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
በወጣቶች ሊግ አስተባባሪነት ምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል የወጣቶች ንቅናቄ መድረክ መካሄዱን በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የወጣቶች ሊግ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ስመኘው አድኖ በአገር ዓቀፍ ደረጃ እየተካሄደው የምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ዛሬ በሲዳማ ክልል ሁላ ወረዳ ሀገረ ሰላም ከተማ ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ በላይ ወጣቶች በተገኙበት ለብልጽግና ፓርቲ የድጋፍና የንቅናቄ ሰልፍ መካሄዱ ተገልጸዋል፡፡
በዕለቱ የተገኙ ወጣቶች ሀገራችንን የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ምርጫቸው ብልጽግና ፓርቲ መሆኑን በመግለጽ ከብልፅግና ጎን መሆናቸውን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት አረጋግጠዋል።

Leave a Reply