You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ…

ብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ…

  • Post comments:0 Comments

ብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ ሀላፊነትን የተሸከመ ፓርቲ ነው፡፡ የተሸከመውን የህዝብ አደራ መወጣት የሚያስችሉ በሳልና ጊዜውን የዋጁ አመራሮችንም ስለመያዙ ጥርጥር የለውም፡፡ከላይ እስከ ታች ያለው የፓርቲው አመራር ሀገራዊ እሴቶችን በተሟላ መልኩ ለማስቀጠል ትልቅ ኃላፊነት የተሸከሙ ጽኑ አመራሮች ናቸው፡፡በትንንሽ ኮሽታዎች የማይደናገጡ ይልቁንም የተጣለባቸውን ህዝባዊ አደራ ለመወጣት መስዋዕት ለመክፈል የተዘጋጁና እየከፈሉ ያሉ የአመራሮች ስብስብ ነው-ብልጽግና፡፡

ከሚለያዩንና ለግጭት ከሚያበቁን መንስኤዎች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ብዙ ሺህ ምክንያቶች አሉንና አንድ ሆነን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የኛን ትርምስ፣የሀገርን የእርስ በእርስ ግጭት ቆመው ለማየት የሚጓጉ ሀይሎች በአንድነታችን አንገታቸውን ልናስደፋቸው ይገባል፡፡አቅጣቻችን ወደፊት ብቻ ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ