You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ ራሱን…

ብልጽግና ፓርቲ ራሱን…

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በአዳዲስ አስተሳሰቦች እየለወጠ፣ወቅቱ የሚጠይቀውን አገርን የመምራት ጥበብ በመላበስ ሀገርን ከፈተና ማቅ አውጥቶ ከድህነት ወደ ብልጽግና ማማ ለማሻገር እየታተረ የሚገኝ ወቅቱን የዋጀ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡
 
ምንጊዜም የኢትዮጵያን ስኬቷን ሳይሆን ውድቀቷን፣ከፍታዋን ሳይሆን የቁልቁለት ጉዞዋን፣ጥንካሬዋን ሳይሆን ድክመቷን የሚመኙ እንቅልፍ የሌላቸው ጠላቶች ህዝቦቿን ሲሻቸው በብሔር አሊያ በሃይማኖት በመከፋፈል የማያባራ የግጭት ቅርቃር ውስጥ ለማስገባት ሲኳትኑ ዛሬም ድረስ አስተውለናል፡፡ ዳሩ ከፍላጎት የዘለለ መቼም የማይሳካ ሕልም ብቻ ቢሆንም፡፡ይህ መሆን የሚችለው ግን በጋራ ከእኩይ ድርጊታቸው መመከትና መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡
 
ሁሉም ሐይማኖቶች፣ሁሉም ብሔሮች… ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚኖሩባት ለዜጎቿ የምትመች አገርን ለመፍጠር ብልጽግና ፓርቲ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ እየሰራ ይገኛል፤የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣የወጣቶችን እና የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ