ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በደብሊው ኤ ኢንደስትሪያል የምግብ ዘይት ኮምፕሌክስ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
• አንድነታችን እንደዘመኑ ጀግንነት በብልጽግና ላይ መደገም እንዲችል ምክንያት ፌስቡክ ነው፣ ዩቲዩብ ነው፣ እያልን በረባው ባልረባው እንዳንጋጭ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ።
• የፋብሪካው ባለቤት ከሰራው ፋብሪካ በላይ ያለውን ለማካፈል ባለው ፍላጎት ምስጋና ይገበዋል፤ ይህ ልባም ባለጸጋ መስራት ብቻ ሳይሆን መካፈልን አስተምሯል።
• አትዮጵያ ሶስት ወሳኝ ምሰሶዎች አሏት፤የመጀመሪያው ምሶሶያችን ፈጣሪ ነው፣ ሁለተኛው ኢትዮያን ለማልማት ወደኋላ የማይለው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ሲሆን ሶስተኛው በፈጣሪ የተሰጠን አንጡራ ሀብታችን ነው።
• እነዚህ ሀብቶች ማልማት የሚችል ህዝብ ልበ ብርሃን የሆነ ህዝብ እና ፈጣሪውን የሚፈራ ህዝብ ስንሆን ኢትዮጵያ የሚገዛትም የሚያስቆማትም ኃይል በምድር ላይ አይኖርም።
• የእኛ የኢትዮጵያዊያን ዋና አደጋ የፈጠረንን አምላክ አላማውን ስተን መጣላት ስንጀምር የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲያጣ ፣ የኢትዮጵያ ሀብት እና ጸጋዎች ማልማት ሲሳነን የሌሎች መሳለቂያ እንሆናለን።
• ኢትዮጵያዊያን ፈጣሪ እንዳለን እና አንድ መሆን እንዳለብን እንዲሁም ተዝቆ የማያልቅ ሀብት እንዳለን ከተገነዘብን ግን ለዓለም ምሳሌ እንሆናለን እንጂ የማንም ሀገር መፈንጪያ አንሆንም።
• አንድነታችንን፣ ፈጣሪያችንን እንዲሁም ሀብታችን ደግሞ እንዲህ አድርጎ የሚያለማ ባለጸጎችን እንዲያበዛልን መትጋት ይኖርብናል።
• ሁለት ልበ ብርሃኖች በሁለት ወር አይተናል፤ ጎጃም ውስጥ ብዙ ሺህ ልበ ብርሃኖች እንዲፈጠሩ እንመኛለን።
• ስንፍናን በማይወዱ ተግተው በሚሰሩ ሀገራቸውን በሚወዱ አሁን አንበሳ መግደል ሳይሆን ኑሮን ማሸነፍ ነው ጀግና የሚያሰኘው ።