የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ አዲስ ድህረ-ገፅ ማብሰሪያና የምርጫ ቅስቀሳ ግብአቶች ማስተዋወቂያ መርሀ-ግብር አካሄደ 

የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ አዲስ ድህረ-ገፅ ማብሰሪያና የምርጫ ቅስቀሳ ግብአቶች ማስተዋወቂያ መርሀ-ግብር አካሄደ 

  • Post comments:0 Comments
የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ አዲስ ድህረ-ገፅ ማብሰሪያና የምርጫ ቅስቀሳ ግብአቶች ማስተዋወቂያ መርሀ-ግብር አካሄደ
የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ በስድስተኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የሚወዳደርበትን አርማና ለምርጫው ያዘጋጃቸውን ቁሳቁሶችን ትላንት ማምሻውን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ አስተዋውቋል፡፡
በእለቱም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መብራቴ ገብረየስ ፓርቲው በዚህ ምርጫ በህዝቦች ይሁንታን አግኝቶ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ እንደሆና ለሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በተሻለ አማራጭ በማቅረብ ተቀባይ ለመሆን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ድሬዳዋ ከዚህ በፊት የምትታወቅበትን የአብሮነትና የፍቅር እሴትን ለማሳደግ ፓርቲው ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነትን መርሁ ማድረጉንና ለምርጫው ውጤታማነትም በድሬዳዋ ብዙሀኑ በሚናገርባቸው ሦስት ቋንቋዎች የምርጫ ቅስቀሳ ስራ መጀመሩን በእለቱ አቶ መብራቴ አስታውቀዋል፡፡
የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ፓርቲው ራሱን የሚያስተዋውቅበት በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በአፋን ሱማሌ ሙዚቃዎችን ከማዘጋጀቱም ባለፈ ራሱን በዲጂታል ሚዲያ ለማስተዋወቅ ያበለጸገውን አዲስ ድህረ-ገፅ ይፋ ማድረጉንና ሌሎች የህትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት እስከ ሰኔ 9 ድረስ በስፋት የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ያበለጸገውን ድህረ-ገፅና የምርጫ ቁሰቁስ ግብአቶችን ባስተዋወቀበት መርሃ ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህና ሌሎች የካቢኔ አባላት፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በእለቱ ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply