You are currently viewing በአገራችን የተጀመሩ የልማት…

በአገራችን የተጀመሩ የልማት…

  • Post comments:0 Comments
በአገራችን የተጀመሩ የልማት ፕሮጅክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ፣ በጀትና የጥራት ደረጃ ተረባርቦ በማጠናቀቅ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ መንግስት በልዩ ትኩረት ይሰራል፡፡ ይህም የፕሮጀክት ተቋራጮችን፣ አሰሪዎችን፣ አማካሪዎችንና የህብረተሰቡን ርብርብና ትብብር የሚጠይቅ ሥራ በመሆኑ ሁላችንም የሚጠበቅብንን መወጣት አለብን፡፡
 
በተለያዩ የአለም ክፍሎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አምባሳደሮቻችንና ዲፕሎማቶቻችን ከምንም ጊዜ በላይ የአገራችንን ጥቅምና ክብር የማስጠበቅ ታሪካዊ አደራ ተጥሎባችኋል፡፡
 
በውጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ህልውናና ሉዓላዊነት የሚጎዱ ጫናዎች በተበራከቱበት በዚህ ወቅት ያለልዩነት ለጋራ አገራችን በጋራ በመቆም ለክብሯና ለህልውናዋ ዘብ የምትቆሙበት ጊዜ አሁን ነው፡፡
 
ሁሉም ፖለቲካ አመራሮች ምንም ያህል የውስጥ ልዩነትና ችግር ቢኖር ሁሉም የሚሆነው አገር ስትኖር ነውና ልዩነቶቻችንን በሰከነ መንፈስና በውይይት እየፈታን አገራዊ ተልዕኮዎች ላይ በማተኮር ጠንካራና ለየትኛውም ጫና የማትንበረከክ አገር ለመፍጠር ተባብረን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡
 
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCDjrabrExOjDbogAkeOUI5w
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ