ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና…

ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና…

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በልጆቿ ብርታት አጠናክራ ቀጥላለች፤ማንም የራሱን የፖለቲካ አጀንዳ ከአገርም ሆነ ከሕዝብ ሊያስበልጥ አይችልም፡፡
የትኛውም ሃይል ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ ሊያወርደን አይደለም ትልቁን የኢትዮጵያዊነት ምሥል እንዲያደበዝዝ አንፈቅድለትም፤ምክንያቱም ሃገር ከምንም ትልቃለች፡፡በሃገራዊ አንድነት ጥላ ስር ተሰብስበን ለሃገራዊ ለውጥ የምንተጋበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
ለዘመናት በተካሄደ ትግል በልጆቿ በተገነባች ኢትዮጵያ ውስጥ በዴሞክራሲና በነፃነት እየኖሩ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እገዛ ከማድረግ እና የብልጽግና ጉዟችንን ከማፋጠን ይልቅ ከውስጥም ከውጭም በባዕዳን ነዋይ ተደልለው በገዛ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ላይ የጸረ-አንድነት መፈክር ሲያሰሙ ተመልክተናል፡፡ሆኖም ግን ብልጽግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጎልበት ለእንደዚህ አይነቱ ተራ የእልቂት ነጋሪት ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ጥላቻን በጥላቻ ሳይሆን ማሸነፍ የሚቻለው ጥላቻን በፍቅር እንደሆነ ብልጽግና ፓርቲ ያምናል፡፡
ብልጽግና በፈተና ውስጥ አልፎ ነገን ለድል የሚበቃ የአሸናፊነት ተምሳሌት እና ሰፊ የህዝብ መሰረት ያለው መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው የሚገባ እውነት ነው፡፡ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ከፍታ የማሸጋገር ሂደቱ በኢትዮጵያዊያን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

Leave a Reply