የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት…

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት…

  • Post comments:0 Comments
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ያዳበረውን ፍቅር፣ መከባበርና መደጋገፍ እንደገና ወደነበረበት በማስቀጠል አንዱ ጎታች ሌላው ተጎታች ሳይሆን ወይም አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆን ሁሉም እኩል ለሀገሩ ብልፅግና አሻራውን የሚያሳርፍበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ለሁሉም ዜጎቿ እኩል የሆነችና የምትመች ዴሞክራሲያዊት አገር እንድትኖር በጋራ ጉዳዮች ላይ በነፃነት በመነጋገር ዴሞክራሲን በተግባር ማረጋገጥ ተችሏል ፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ከማንም የተደበቀ አጀንዳ ኖሮት አያውቅም፤አጀንዳችን ልማት ነው፤አጀንዳችን ብልጽግና ነው፤አጀንዳችን ትክክለኛ ፌደራሊዝም እንዲተገበር ማድረግ እና ዴሞክራሲን መትከልና ማጽናት ነው ፡፡
ትንንሽ ልዩነቶቻችንን በማቻቻል፣ ከጽንፈኝነት፣ከጎጠኝነትና ከቡድንተኝነት አስተሳሰብና ድርጊት በመውጣት እና ለሃገርና ለሃገራዊ አንድነት ቅድሚያ መስጠት ከቻልን በእርግጥም የበለጸገች ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ነገን ተሻግሮ ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ ፓርቲው ለአገርና ለህዝብ የማይከፍለው መስዋዕትነት የለም፡፡ምክንያቱም ሀገር ከሁሉም ትልቃለችና፡፡

Leave a Reply