• Post comments:0 Comments

ኢትዮጵያውያን የቱንም ያህል የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖርብንም ልዩነቶቻችንን አቻችለን፣ አጥብበን፣ የቆዬ የመደማመጥ ባህልንም አዳብረን ሀገራችንን ከየትኛውም ዓይነት ጠላቶቿ ከደገሱላትና ከሚደግሱላት የውድቀትና የጥፋት አደጋ በጋራ ልንጠብቃት ይገባል ፡፡

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንዳይሆን በማነህ ማነህ ትንቅንቅና በከፋ ጥላቻ ተውጦ እርስ በርስ በሚፈጠር መናቆርና መባላት ሀገሪቷን ለውጭ ጠላቶች የተመቸች ሲሳይ አድርጎ ላለመስጠት ሁሉም ዜጋ በተናጠልም ሆነ በወል እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡

ከራሳችን የውስጥ ችግር ባሻገር ከአገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያ ጠል ጠላቶች የሚሠሩት ሴራ የእርስ በርስ ግጭት እንዲነሳ፣ የጎሳና የዘር ጥላቻ እንዲዛመት ወደ ግጭት እንዲያመራ እና አገር ህልውና እንድታጣ ብሎም ሉዓላዊነቷ እንዲደፈር በመሆኑ ይህንንም ማወቅና መከላከል ይገባል፡፡

አይታክቴዋ ግብጽና ተላላኪዎቿ ኢትዮጵያን ለማተራመስና ለማበጣበጥ መቼም ሆነ መቼ ተኝተው አያውቁም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይሁን እንጂ አይበገሬዋ ኢትዮጵያም ሴራቸውን ለማክሸፍ ሰንፋ አታውቅም። መቼም ቢሆን ሉዓላዊነታችንን አስደፍረን አናውቅም፤ኢትዮጵያዊያን ከመንግሥት ጎን በመሆን የጋራ ጠላቶቻችን አንገት ማስደፋትና ልማቶቻችንን ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ

Leave a Reply