የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት…

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት…

  • Post comments:0 Comments
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ያስተሳሰረው የሰላም፣ የአንድነትና የፍቅር ገመድ በሴረኞችና በተላላኪዎቻቸው አማካኝነት እንዳይበጠስ ምን መደረግ አለበት የሚለው ሃሳብ በሁላችንም አዕምሮ ውስጥ ሊኖር ይገባዋል፡፡ይህ ኩሩና ጨዋ ሕዝብ ከሚጠቀሱለት የጋራ እሴቶች መካከል ዋነኛው ለአገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር ነው፡፡
ይህ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የዘመናት እሴት ሊከበር ይገባል፡፡
 
ኢትዮጵያ የምትባለው የጀግኖችና የጨዋ ኢትዮጵያውያን አገር ለዘመናት ከውጭ ወራሪዎች ቢፈትኗትም ከውስጥ ሴረኞች አገርን ለማተራመስ እንቅልፍ አጠው ቢኳትኑም ከቶውንም አልተሳካላቸውም፡፡ይህች ታሪካዊ የጀግኖች አገር ህልውናዋ አስተማማኝ ሆኖ እስካሁንም የቀጠለው በህዝቦቿ ጽኑ ተጋድሎ እና የጠነከረ የአገር ፍቅር ስሜት ነው፡፡
 
ማንኛውም የፖለቲካ ፍላጎት ወይም ጥቅም ከአገር በላይ ሊሆን አይችልም፤ሆኖም አያውቅም፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምንም ነገር በላይ የሚያሳስበው የአገሩ ጉዳይ ብቻ ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ይህንን ሕዝብ ማክበር የግድ ያስፈልጋል፤ምክንያቱም ከአገር በላይ ምንም የለምና፡፡
 
እያንዳንዱን ጉዳይ ፖለቲካዊ ገጽታ በማላበስ በውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ ሙከራ ፍጹም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ኢትዮጵያ ራሷን የቻለች ሉዓላዊት አገር በመሆኗ የምትመራበት ህግና ስርዓት አላት፡፡የውስጥ ጉዳዮቻችንን በራሳችን እንፈታለን፤የማንንም ድጋፍም ሆነ ይሁንታ አያስፈልገንም፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲ ይምረጡ
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCDjrabrExOjDbogAkeOUI5w

Leave a Reply