You are currently viewing የወላይታ ሶዶ ከተማ እና የአረካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የወዳጅነት ጨዋታ ተካሄደ

የወላይታ ሶዶ ከተማ እና የአረካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የወዳጅነት ጨዋታ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
የወላይታ ሶዶ ከተማ እና የአረካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የወዳጅነት ጨዋታ ተካሄደ
 
በአረካ ከተማ አስተዳደር የወላይታ ሶዶ እና የአረካ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አባልና ደጋፊ የሆኑ የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታ በአረካ ስታዲየም ተካሂዷል።
ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የክልልና የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የወዳጅነት ጨዋታ እንድሁም የይምረጡኝ ምርጫ ቅስቀሳ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
 
በፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ብሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፤የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ዶክተር እንድርያስ ጌታ፤የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀን ጨምሮ ለሎች የዞንና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
 
ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል በተደረገው የወዳጅነት ጨዋታ የሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ 2ለ1 በሆነ ወጤት የአረካ አቻውን አሸንፏል።
 
በጨዋታው እጅግ ወንድማማችነት እንዳዩ እና ብልጽግና ፓርቲ በህብረብሔራዊነት የሚያምን መሆኑ ጨዋታውን የታደሙት አንድ አንድ አካላት ገልፀዋል።
መደመር መንገዳችን ብልጽግና መዳረሻችን ነዉ!
#ብልጽግናን ይምረጡ!
#አምፖልን ይምረጡ!
 
#የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ምላሽ ይስጡ