የብሔር ማንነት እና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ…

የብሔር ማንነት እና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ…

  • Post comments:0 Comments
በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ ብልጽግና አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ፓርቲያችን ሲነሳ የሀገራችን ፖለቲካ የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ በመገንባት ሰላም፣ዴሞክራሲ፣ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣የዜጎች ክብር፣ፍትህና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር እንድትሆን ያለፈውን ጥፋት በይቅርታ መጪውን ጊዜ በብሔራዊ መግባባት እና ዴሞክራሲያዊ ድርድር በማድረግ ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት እንደሚያስፈልግ በጽኑ በማመን ነው፡፡
 
በመሆኑም በፖለቲካው መስክ የብሔር ማንነት እና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ በዘላቂነት የሚያስኬድ የሀገርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ማስኬድ ያስፈልጋል፡፡ህብረተሰብን በጎራ በመክፈል አግላይ የነበረው አካሄድና አደረጃጀት አቃፊና አካታች በሆነ ብሎም የሀገራችንን ተጨባጭ የፖለቲካ ችግር በሚፈታ ማዕቀፍ ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡
 
ፖለቲካዊ ብልጽግናችን ሁሉን አቀፍ ማህበረሰብ ለመገንባት የምናደርገውን ጥረት የሚደግፍና አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት ትልም ያለው እንዲሆን ይሰራል፡፡
 
ሀገራችን ለሁላችንም ትበቃለች የሚል ጽኑ ሃሳብ በመያዝና የዕጦት አስተሳሰብን በመሻገር ለሁሉም ዜጎች የምትሆንና ሁሉም በኩራትና በምቾት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ትግል ያደርጋል፡፡
 
ተጨማሪ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCDjrabrExOjDbogAkeOUI5w
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

Leave a Reply