You are currently viewing ሃይማኖቶቻችን ለሰላም፣ሰላም ለሀይማኖቶቻችን  /በሚራክል እውነቱ/

ሃይማኖቶቻችን ለሰላም፣ሰላም ለሀይማኖቶቻችን /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ የህዝቦችና የዜጎች የመቻቻል፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት ሆና ለዘመናት ጠብቃ የቆየች ሀገር ናት፡፡ ይህ የመቻቻልና የአብሮነት ባህል በተለይ በተለያዩ ሃይማኖቶች ግንኙነት ጎልቶ የታየ ከመሆኑ አንጻር በዚህ ረገድ አገራችን በብዙ ሀገሮች ዘንድ በምሳሌነት እንድትጠራ አድርጓታል፡፡
የመተሳሰብና የአብሮነት እሴታችን የዘመናት ሂደት ውጤት ሆኖ ወደዚህ ትውልድ መድረስ ችሏል፡፡ ይኸውም መሠረታዊ ባህርይ ሆኖ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በቅብብል የመጣ የመቻቻል ባህል ነው፡፡በተለያዩ እምነት ተከታዮች በሰላም አብሮ መኖርን አስመልክቶ ሁሉም አወንታዊ የሆነ አመለካከት አላቸው፡፡
ይኸውም በተለይ የአይሁድ፣ የክርስትናና እስልምና የሰው ልጅ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ ክቡር ነው የሚል እምነት አላቸው ሁሉም ሰው በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ስለሆነም እኩል ነው፡፡ ክብርም አለው ብለው ያምናሉ በተጨማሪም ሁሉም እምነቶች ሰላምና ፍቅር በጣም አስፈላጊ እንደሆነም ያምናሉ፡፡
ብዙውን ጊዜ የሃይማኖት መቻቻል ሲባል ቀድሞ ወደ አዕምሯችን የሚመጣው አሉታዊ እንደሆነ ቢመስለንም ትርጉሙ ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሌላውን መቀበል መውደድ እምነቱን ሕይወቱን ክብሩን መንከባከብ እንዲሁም ተስማምቶ ተግባብቶ ተሳስቦና ተረዳድቶ ሕይወትን መምራት ማለትን ሊያመለክት እንደሚችል በዘርፉ ከተፃፉ ሰነዶች መገንዘብ ይችላል፡፡
የሃይማኖት መቻቻል ማለት የሌላውን ሰው ሃይማኖት ትክክል ነው አይደለም ወደሚለው ድምዳሜ ወይም ግምገማ ውስጥ ሳይገባ ከኔ የተለየ አመለካከት ወይም እምነት መኖር ይችላል አብረን መኖር እንችላለን የሚል አመለካከት ነው፡፡
በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች በሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት ለምሳሌ ጥምቀት፣ኢድ አል ፈጥር፣መስቀል፣መውሊድ…በመሳሰሉት ሁሉም ምዕመናን የየራሰቸውን ዕምነትና ሀይማኖት በሰላም ተጀምሮ በፍቅር ይጠናቀቅ ዘንድ ፍላጎታቸው ነው፡፡ለዚህም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልዩ ልዩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ሲከበሩ ምንም አይነት ኮሽታ ሳይሰማባቸው በሰላም እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን የማስተባበሩን ሚና እየተወጡ የሚገኙት፡፡
በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወጣቶችና ሌሎች ምዕመናን ከበዓሉ አስተባባሪ ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን በማስተባበር ሀላፊነታቸው ሲወጡ እናያለን፤የኢድና መውሊድ የመሳሰሉ በዓላት ሲከበሩም ቢሆን የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፊት ሆነው የማስተባበሩን ሚና ሲወጡ ማስታዋል ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን አዲስ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የሃይማኖትን ብዝሃነትን በማስተናገድ የዘመናት ታሪክ ላላት ኢትዮጵያ አብሮ የመኖር ባህላችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ዕሙን ነው።
ሁላችንም የየራሳችን የምንከተለው ዕምነትና ሀይማኖት ይኖረናል፤ሁሉም ዕምነቶቻችን ደግሞ ሰላም ፣ፍቅርን ፣መቻቻልንና እርስ በእርስ መከባበርን አጥብቀው ያስተምራሉ፡፡ለዚህም ነው ሁሉም ሀይማኖቶች ለሰላም ያላቸው ሚና የጎላ ነው የሚባለው፡፡
ጠላቶቻችን ሀገሪቱን ያለ ህዝብ ለማስቀረት እና የማያቋርጥ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የውጭ ሀይሎች እጃቸውን አስገብተው የፈለጉትን እንዲያደርጉ እንቅልፍ አጠው ይሰራሉ፡፡ብሔር እና ሐይማኖት ደግሞ ህዝብን ለማወክ እንደ መሳሪያ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ጠላቶቻችን የቱንም ያህል ቢሰሩ እኛ ግን የቆዬ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ተጠቅመን አንድነታችንን እናሳያቸዋለን፤መከባበራችንን በተግባር ይታያል፡፡
ከቀናት ኋላ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ እና ለአንድ ወር በጾምና በጸሎት ያሳለፉት የሙስሊም ወንድም አህቶቻችን በደስታና በፍቅር እንዲያሳልፉት በዓሉ በዓላችን ነው ብለን በሰላም እንዲከበር ከወዲሁ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰራ ይገባዋል፡፡ምክንያቱም ሰላም የሁሉም ፍላጎት ነውና፡፡
እንዲህ ስንሆን ኢትዮጵያዊነታችን ጎልቶ ይታያል፤አንድነታችን የበለጠ ይጠነክራል፤በፍርቅ ጥላ ስር መሰባሰባችን ለወዳጆቻችን መረቅ ለጠላቶቻችን ደረቅ መሆናችንን ማሳያ፣በዓሉን በየኔነት ስሜት በሰላም እንዲከበር ማድረግ የእርስ በእርስ ግንኙነታችንን ከማጠናከሩም በላይ ሀገራዊ ስሜት ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡
ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያሳኛት ኦሮሞው፣ አማራው፣ ትግሬው፣ ሶማሌው፣ ሲዳማው፣አፋሩ፣ጉሙዙ፣ሀድያው፣ወላይታው፣ከምባታው፣ጉራጌው፣ጋምቤላው፣ድሬው፣ሀራሬው በጥቅሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው የሁሉም እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተደምሮ ነው፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ