በፈተናዎች መካከል ድሎች አሉ /በሚራክል እውነቱ/

በፈተናዎች መካከል ድሎች አሉ /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments
እንደ ሃገር ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ በርካታ ተግዳሮቶች ተከስተው አልፈዋል፡፡ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣በርካታ ወገኖቻችንን በተከሰቱ ሁከቶችና ብጥብጦች በሞት አጠናቸዋል፤ስደት እና እንግልት ደርሶባቸዋል፡፡
እርግጥ ነው ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር አንድነታችንን የሚሸረሽሩ በርካታ ጉዳዮጭ ገጥመውናል፤ ለዘመናት የቆየውን አብሮነታችንን አደጋ ላይ ሊጥሉት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ሰርተዋል፤ ከኢትዮጵያዊነት ማማ ላይ ወርደን በመንደር ጠበን እንድንኖር ለፍተዋል፣ጥረዋል ግን አልተሳካለቸውም፡፡
እርስ በእርሳችን እንድንበላላ ሲሻቸው በብሔር አሊያም በሐይማኖት ግጭት ቀስቃሽ ሃሳቦችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላት ፎርሞች በመልቀቅ በማህበረሰቡ መካከል መጠራጠርን ፈጥረዋል፡፡
ሀገር ህልውናዋ አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው ሰርተዋል፤ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመፈጸም አንዱ ብሔር በሌላው ላይ እንዲነሳና ወደማያባራ ትርምስ ለማስገባት ጥረት አድርገዋል፤ግን ፈጽሞ አልተሳካላቸውም፡፡
ግብጽ ኢትዮጵያ ሰላም ውላ እንድታድር መቼም አትፈልግም፣ይህ ለዘመናት የነበረ ሐቅ ነው፡፡ውስጣዊ አለመረጋጋቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ እየቆጠሩ በእሳት ላይ ቤንዝን ለማርከፍከፍ እንቅልፍ የላቸውም፡፡እርግጥ ነው እንዲህ አይነቱን ድርጊት ግብጽ ብቻዋን ፈጽማ አታውቅም ፤ይልቁንም በሀገር ውስጥ በሚገኙና በጥቅም ህሊናቸውን አሳላፈው ከሸጡ እፉኝቶች ጋር በመሆን እንጂ፡፡
በመጪው ግንቦት ወር ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን ስድስተኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከወዲሁ ለማደናቀፍ የውስጥ አሸባሪዎቹ ህወኃትና ሸኔ በውጭ ከሚገኙ ሀይሎች ጋር ስራቸውን ጀምረዋል፡፡ግብጽም ብትሆን በታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ግትርነት ዓለም ያውቀዋልና በገንዘብና በልዩ ልዩ መልኩ ለሸኔና ለህወኃት ድጋፍ ማድረጓ አይቀርም፤ ግን ግን መቼም አይሳካላቸውም፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን በውስጥ ጉዳያችን ላይ ማንም ጣልቃ እንዲገባ አንፈቅድም፡፡የውስጥ ጉዳዮቻችንን በዛፍ ስር ጥላ ተወያይተን ለችግሮቻችን መፍትሔ ስንመካከር ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡
እያበላችና እያጠጣች ያሳደገች አገር፣ስንታረዝ ያለበሰችና ያስተማረች አገር ውድቀቷን መመኘት ምን የሚሉት የዋህነት ነው? በእርግጥ ያለ ፈተና ድል አይገኝም፣ያለ ውድድር አሸናፊነት የለም፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት በርካታ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም ከህዝባችን ጋር በመሆን ሀገራችን ከገጠማት የመፈራረስ አደጋ እንድትወጣና ህልውና እንዲቀጥል ታሪክ የማይረሳው ስራ ሰርቷል፤ምንም እንኳ ውስጣዊና ውጫዊ ቀሪ ፈተናዎችን መወጣት የግድ ቢሆንም፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ዕውነትን ይዞ ህዝብን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር ታሪካዊ አደራ የተጣለበት ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ሃገራዊ አንድነትን፣ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት፣የእርስ በእርስ መተሳሰብን በጥቅሉ የቆዩ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ለመመለስ የሚሰራ ፓርቲ እና እነዚህን ወደ ኋላ ለመመለስ ከሚጥሩ ሃይሎች ጋር ፊት ለፊት የሚታገል የኢትዮጵያዊያን ፓርቲ ነው፡፡
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

Leave a Reply