You are currently viewing ኢትዮጵያን በጋራ ክንዳችን…

ኢትዮጵያን በጋራ ክንዳችን…

  • Post comments:0 Comments

በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያንዣበበው ጥቁር ደመና ተገፎ የሰላምና የአንድነት አየር የሚንፍስበት ወቅት ሩቅ አይደለም፡፡በአጭር ጊዜ የተመለከትነው የለውጥ ወጋገን ተጠናክሮ ይቀጥል፣እዛና እዚህ የከበቡንን የጋራ ጠላቶቻችንን አንገት ለማስደፋት፣የምንወዳት ሃገራችንን ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃናማዋ ኢትዮጵያ ለመቀየር፣ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር የምትችል እና ተሰሚነቷ ያደገች ሀገርን ለመገንባት የእርስ በእርስ አንድነታችንን ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው መፍትሔ ነው፡፡

በጋራ ተቻችለንና ተከባብረን፣ በአንድነትና በፍቅር ተዛምድን ነጋችንን በብርሀን ፍንጣቂ ለማድመቅ የእኔና የእናንተ የጋራ አንድነት፣እርስ በእርስ መደማመጥ ያስፈልጋል፡፡

ዛሬ ሃገራችን ኢትዮጵያ በርካቶች እንደ ንስር አሞራ እያንዣበቡ ከተያያዘችው የብልጽግና ጎዳና ለማስወጣት እና ዛሬም እንደትናንቱ በእጅ አዙር ቅኝ ለመግዛት ጥረት ቢያደርጉም ጠላቶቻችንን አንድ ሆነን በማሳፈር የጀመርነውን ሃገራዊ ለውጥ እናስቀጥላለን፡፡

ለእኛ ከማይመጥኑን አሮጌ አስተሳሰቦች፣ትስስራችን ከሚያላሉ ኋላ ቀር የኔነት አመለካከቶች ራሳችንን አርቀን በእኛነት መንፈስ ለጋራ ለውጥ በጋራ የምንታትርበት ወኔ ለመላበስ ራሳችንን ልናዘጋጅ የግድ ይላል፡፡እርስ በእርስ በጥርጣሬ መንፈስ ሆነን እንድንኖር የሚፈልጉ ከውስጥም ከውጭም ያሉ ሃይሎች ይኖራሉ፡፡

ኢትዮጵያን በጋራ ክንዳችን የተገነባች የጋራችን ቤት አድርገን ለመስራት ከሰሜን እሰከ ደቡብ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዮጵያን በጠንካራ አለት ላይ መሰረቷን ለመገንባትና የጋራ አንድነታችንን ለማጥበቅ፣ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ለዓለም የምናስመሰክርበት ይሆን ዘንድ ሌት ተቀን ለመስራት ብልጽግና ፓርቲ ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ