ለምንወዳት ሃገራችን ስንል በጋራ ልንቆም…

ለምንወዳት ሃገራችን ስንል በጋራ ልንቆም…

  • Post comments:0 Comments
ሃገራችን ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት የተጋረጠባትን ሁለንተናዊ ፈተና ተቋቁማ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ብትችልም የዶሮ ያህል እንቅልፍ የሌላቸው ጠላቶቻችን ግን አሁንም ሃገራችን ወደ ፊት እንዳትራመድ እንቅፋት ሆነውባታል፡፡የቱንም ያህል ፈተናው ቢበዛም ካሰብነው ለመድረስ ግን የሚያግደን አንዳች ሃይል ግን አይኖርም ፡፡
 
የውጭ ጠላቶቻችንም የቱንም ያህል በሃገር ውስጥ ካሉ ጠላቶቻችን ጋር ጋብቻ ቢፈጽሙም አንዳቸውም ግን ወደፊት ከመራመድ አያቆሙንም፡፡ ዋናው ቁም ነገር የውስጥ አንድነታችንን በማጠናከር ወደ ብልጽግና ማማ የምንደርገውን አልህ አስጨራሽ ጉዞ አጠናክረን መቀጠል ብቻ ነው፡፡ ከመንደርተኝነት የጠበበ አስተሳሰብ ወጥተን ትልቁ ሃገራዊ ምስል ላይ ልናተኩር ይገባል፡፡
 
ምሁራን፣ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የሐይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች፣የማህበረሰብ አንቂዎች እና ሌሎችም ለምንወዳት ሃገራችን ስንል በጋራ ልንቆም ይገባል፡፡ይህ ሲሆን ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤትና የዓለም አገራት ጋር የምታደርገው ግንኙነት ውጤታማ ከመሆኑም ባሻገር በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ ተቀባይነትን እንድታገኝ ያስችላታል፡፡ይህ ሂደት ጠላትን መቀነስ ወዳጅን የማብዛት ዘዴ በመሆኑ ካሰብነው የዕድገት ደረጃ ደርሰን ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ ይግዘናል፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

Leave a Reply