ብልጽግና ፓርቲ ዛሬን ሳይሆን ነገን…

ብልጽግና ፓርቲ ዛሬን ሳይሆን ነገን…

  • Post comments:0 Comments

በኢትዮጵያዊያን የጋራ ርብርብ የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የተሠሩና መደገም የማይገባቸውን ስህተቶችን በማረም እንዲሁም ሊያግባቡን በሚችሉ የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በማተኮር ለመጪዉ ትዉልድ ጥቅም የሚተጋ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሚሰራ አገራዊ ፓርቲ ነው፤

የወጣቶችንና የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለፉት አመታት በመላ አገሪቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወጣቶችና ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ራሳቸውን እንዲለውጡ በለውጡ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጦት የሚገኝ አጀንዳ ነው፡፡ ምክንያቱም ሀገራችን በወጣቶችና በሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ የምትገነባና እየተገነባች ያለች ሀገር ናትና፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ዛሬን ሳይሆን ነገን፣ነገን ሳይሆን ዘመናትን ቀድሞ የሚሰራ ባለራዕይ ፓርቲ ነው፡፡በሀገርና በዜጎች ክብር ላይ የሚመጣ በማንኛውም መልኩ ሊታገስ እንደማይችል ለዓመታት እንጀራ ፈልገው በሰው ሀገር በበደልና በስቃይ ያሳለፉ ዜጎቹን ኑ እናት ሀገራችሁ ለሁላችንም ትበቃለች በማለት ወደ ሀገራቸው ማስገባት የቻለ ለዜጎች ተቆርቋሪ ፓርቲ ነው፡፡

የብልጽግና ተምሳሌት የሆነው አምፖል ብርሃን በመምረጥ ሀገራችን ከድህነት ወጥታ ወደ ከፍታ ማማ የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን የሚወዷት ሀገርዎን ዕጣ ፋንታ ይወስኑ፡፡

ብልጽግናን ይምረጡ

Leave a Reply