You are currently viewing የታላቁ ሕዳሴ ግድብ…

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ…

  • Post comments:0 Comments

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ለአገራችን ዜጎች ብሔራዊ መግባባት በመጫር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትንና የትብብር መድረክ የፈጠረ ነው።የታላቁ ህዳሴ ግድብ መሠረት ከተጣለ ጀምሮ የተወሰኑ መሰናክሎች ቢኖሩም ዕድገት እያሳየ ለፍፃሜ እየተቃረበ ነው፡፡

እነ ሜቴክ የዘረፉት ምትክ የሌለሽ ገንዘብ፣ በየቦታው የምናያቸው ግጭቶች፤ ከትህነግ ላይ የተደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻ፣ የሱዳን ድንበር ወረራ እና ዝርፊያ እንዲሁም ባለፈው ዓመት የተነሳው እና ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ሁሉ ግድቡን ለማጣደፍ ለሚደረገው ጥረት ያልፈጠሩት መሰናክል አልነበረም።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈፃፀም 79 በመቶ የደረሰ ሲሆን በዚህም መሠረት የኮርቻ ግድቡ 99 በመቶ፣ የጎርፍ ማስተንፈሻው ወይም ጎርፍ መከላከያ ግንባታ ደግሞ 97 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ 84 በመቶ፣ አጠቃላይ የሲቪል ሥራው ዛሬ ላይ 91.4 በመቶ ተጠናቋል፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የብረታ ብረት ሥራዎች 54 በመቶ መድረስ መቻላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2012 ዓ/ም በክረምቱ ወራት የግድቡ የውሃ ሙሌት ሥራ ማከናወን ተችሏል፡፡በዚህም ሳያበቃ ዘንድሮ ማለትም በ2013 ዓ/ም ሁለተኛውን ሙሊት ስራ ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ድል ነው፡፡ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከሰራቸው ውጤታማ ተግባራት አንዱ የሆነው ግድቡ በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሁለት ተርባይኖች ሀይል በማመንጨት ኢትዮጵያን በብርሃን ይሞሏታል፡፡

 

ብልጽግናን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ