You are currently viewing ብልጽግና ነገን አስቦ ዛሬን እየሰራ ያለ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፤

ብልጽግና ነገን አስቦ ዛሬን እየሰራ ያለ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፤

  • Post comments:0 Comments
ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረገቡበት ወቅት ነው።
 
መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … ነበር። ይህንን ነባራዊ እውነታ ከመቀየር አንጻር ባለፉት ሶስት ዓመታት አያሌ ስራዎችን ብልጽግና ፓርቲ ሰርቷል፡፡
 
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለህዝቡ ተሰፋ ሰጪ ንግግሮችን በማድረግና የተናገሩትን በተግባር በመፈጸም ህዝብን ከተስፋ መቁረጥ ሀገርን ከብተና ታድገዋል፡፡
 
የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን የተረዳው ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት በሀገር ውስጥ በሚያራምዱት ሃሳብና ባላቸው ፖለቲካዊ አቋም የተነሳ ታስረው የነበሩትን መፍታትና በውጭ ሀገራት ተሰደው ይኖሩ የነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡና ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ መንገድ የከፈተ የሚታይና የሚጨበት ስራ የሰራ ሀገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ለዚህ ደግሞ የፓርቲያችን ፕሬዝደንት ዶ/ር አብይ አህመድ ሚና በእጅጉ የጎላ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡
 
ከዴሞክራሲ ምህዳር መስፋት ጋር ተያይዞ ሊጠቀስ የሚችለው ባለፉት ሶስት ዓመታት በበርካታ አካባቢዎች የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው። እነዚህ ሰላማዊ ሰልፎች የተለያዩ አርማዎችና ሰንደቅ ዓላማዎች የታዩባቸውና የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉባቸው ናቸው። ዴሞክራሲ ማለት ትክክል የሆነው ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ ሃሳብም ቢሆን ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ የሚንጸባረቅበትን እድል መፍጠር ነው ብሎ ያምናል ብልጽግና ፓርቲ፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ