You are currently viewing ሩቅ አስቦ – ሩቅ ለመጓዝ የተነሳው ብልጽግና!

ሩቅ አስቦ – ሩቅ ለመጓዝ የተነሳው ብልጽግና!

  • Post comments:0 Comments
ሩቅ አስቦ – ሩቅ ለመጓዝ የተነሳው ብልጽግና!
ኢትዮጵያ በሥነ ፈለክ ምርምር መስክ ተጠቃሽ አገር ነች፡፡ ይህን የአገራችንን ሁኔታ የተገነዘበው የዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ ህብረት፤ በ2011 ዓ.ም በአንድሮሜዳ ህብረ ኮከብ ውስጥ የሚገኙትን አንድ ኮከብና አንድ ኤክሶ ፕላኔት ኢትዮጵያ እንድትሰይም ዕድል ሰጥቶ ነበር፡፡
ስለዚህ አገራችን በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ያላት ተሳትፎ አሁን በሚገኝበት ደረጃ መሆኑ የሚያስቆጨን ቢሆንም፤ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ፓርቲያችን ከተመሠረተ ወዲህ አገራችን ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ሁለት ሳተላይቶችን ወደ ህዋ አምጥቃለች፡፡ አንዳንዶች አንደ ቅንጦት የሚመለከቱት ቢሆንም፤ ፓርቲያችን ብልጽግና የህዋ ሳይንስ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመረዳት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ይገኛል፡፡
በዘመነ ብልጽግና ኢትዮጵያ በ2012 ታህሳስ ወር ETRSS-1 የተባለች የመጀሪያዋን ሳተላይ ያመጠቀች ሲሆን፤ ከአራት ወራት በፊት ደግሞ ሁለተኛዋን ET- SMART- RSS የተሰኘች ሌላ ሳተላይት ወደ ህዋ ልካለች፡፡ ETRSS-1 የተሰኘችው የመጀመሪያዋ ሳተላይት፤ በዘርፉ ባለሙያዎች ‹‹Remote- sensing satellite›› በሚል የምትጠቀስና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያላት ሳተላይት ናት፡፡
ሁለቱም ሳተላይቶች እንዲመጥቁ ሲደረግ 21 ኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች፤ ከቻይና የስፔስ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ባለሙያዎች ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩና በተግባር የተደገፈ ዕውቀትና ልምድ እንዲቀስሙ ተደርጓል፡፡ እየተተገበረ ያለው የሳተላይት ፕሮግራማችን ተቀዳሚ ዓላማም ኢትዮጵያውያን ኢንጂነሮችና ሳይንቲሳቶች ከቻይና ባለሙያዎች ጋር በመሥራት የሳተላይት ግንባታ፣ ማምጠቅና ማስተዳደር ልምድ ለማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸትና በዚህም በዘርፉ አገራዊ አቅም እንዲገነባ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም፤ ዛሬ ወደ ህዋ የተላኩትን ሳተላይቶች፤ ከእንጦጦ የኦብዞርቫቶሪ ስርዓት ጋር በማገናኘት የሳተላይቶቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የማስተዳደር አቅም መገንባት ተችሏል፡፡
ፓርቲያችን ብልጽግና አገር የማስተዳደር ኃላፊነት እንደወሰደ ‹‹የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት›› የተባለ መንግስታዊ ተቋም እንዲቋቋም የመሪነቱን ሚና በመውሰድ ቀደም ሲል ‹‹የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ›› (ESSS) ባፈራቸው በርካታ ወጣት ሳይንቲስቶች ዘንድ ይበልጥ መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡ ሳተላይት የመገንባት አቅምን ጨምሮ፤ አገራዊ የስፔስ ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት እንዲፈጠር ለማድረግ ከፍተኛ ገንዘብም መድቧል፡፡
በዚህ የቀዳሚነት ሚናው የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር ባደረገው የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት መሠረት፤ ስድስት ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባት፤ የመጀመሪያዋ፤ ‹‹Remote- sensing satellite›› ለመንግስትና ለሌሎች የምርምር ተቋማት የተለያዩ መረጃዎችን የምታቀርብ ሳተላይት ልኳል፡፡ በመሬት ላይ ቅኝት በማድረግ ለሲቪል አገልግሎት የሚውሉ መረጃዎችን የምትልከው ይህች ሳተላይት፤ የአካባቢ ሁኔታን ለመከታተል፤ የግብርና ሥራዎችን በአግባቡ ለማቀድና የአየር ጠባይ አዝማሚያዎችን ለማጥናት፤ እንዲሁም ድርቅ ሲከሰት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት፤ ብሎም የማዕድን ሥራዎችን ለማከናወን እገዛ ታደርጋለች፡፡
በብልጽግና የአመራር ዘመን ዛሬ ኢትዮጵያ ሳተላይት ካላቸው 11 አፍሪካ አገራት አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ ከአንድ ዓመት በፊት (በጀንዋሪ 2020 ) መንግስት የሳተላይት መፈብረኪያ፣ መገጣጠሚያ፣ ማቀናጃ እና መሞከሪያ (MAIT) ተቋም ግንባታ ሥራን ለማከናወን፤ ‹‹ኤሪያን ግሩፕ›› (Ariane Group) ከተሰኘ አንድ የፈረንሳይ የስፔስ ኩባንያ ጋር መፈራረሙም ይታወቃል፡፡
ታላቋ አገራችን ሳተላይት በመገንባትና በማስተዳደር (ኦፕሬሽን) ረገድ ራሷን ለመቻል የሚያበቃትን አገራዊ አቅም የመገንባት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያላት በመሆኑ፤ ከአራት ወራት በፊት ሁለተኛዋን ሳተላይት አምጥቃለች፡፡ ይህች ሳተላይት ከፍተኛ ሪዞሉሽን ያለው ምስል መላክ የምትችል ሳተላይት ስትሆን፤ ሌላ ለብሮድካስትና ለንግድ የቴሌኮም አገልግሎት የምትሰጥ ሦስተኛ ሳተላይት ለማምጠቅ ስምምነት የተፈራረመችው ብልጽግና ለቴክኖዎሎጂ ባለው ትኩረት ነው፡፡
ኢትየጵያ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ስታስወነጭፍ በህዝብ ዘንድ የተፈጠረውን ዓይነት ልዩ ስሜት የፈጠረ ሌላው ጉዳይ አገራችን ‹‹የደመና ማበልጸግ›› ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆኗ መገለፁ ነው፡፡ ይህ ‹‹የደመና ማበልጸግ›› ቴክኖሎጂ፤ ደመናን በማሰባሰብ ዝናብ ማዝነብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሲሆን አሜሪካንና ካናዳን ጨምሮ በ52 አገራት ጥቅም ላይ የዋለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ኢትዮጵያም የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን መደረጉ፤ ፓርቲያችን ብልጽግና የነገዪቱን ኢትዮጵያ እያሰበ ለቴክኖሎጂ የሰጠውን ልዩ ትኩረት አመላካች ነው፡፡
ይህ ‹‹የደመና ማበልጸግ›› ቴክኖሎጂ፤ ፓርቲያችን ቴክኖሎጂን በመጠቀም በግብርና ዘርፍ ያለውን አሰራርና ምርታማነትን ለማሻሻል የያዘው ዕቅድ አንድ አካል ተደርጎ የሚወሰድና ብልፅግና የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ በአጭር ጊዜ የመቀየር ብቃት ያለው ፓርቲ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ቴክኖሎጂው በደመና ውስጥ እርጥበት እንዲፈጠርና ዝናብ እንዲዘንብ ለማድረግ ያሚያስችል በመሆኑ፤ ምርታማነትን በማሳደግ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነው የአገራችን የግብርና ልማት እንዲሳለጥ የሚያደርግ ነው፡፡ አሁን የሚታየውን ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ዕድገት የሚመጥን የግብርና ምርት ለማምረት ከማስቻል ባሻገር፤ ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ምርት ለማምረትና ለኑሮ አመቺ ያልሆኑ አካባቢዎችን ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያግዝም ቴክኖሎጂ ነው፡፡
እንደሚታወቀው፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ግብርና ለአየር ንብረት ለውጥ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ እናም በቂ የደመና ክምችት ያላት አገራችን በዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቅማ ዝናብ ለማግኘት የምትችልበት ሰፊ ዕድል በዘመን ብልጽግና ተፈጥሯል፡፡ የቴክኖሎጂው ፋይዳ የግብርና ምርትን በማሳደግ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ዜጎች ንፁህ የመጠጥ ውሃን ጨምሮ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል ውሃ ለማግኘት የሚችሉበትን ዕድልም መፍጠር ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ቴክኖሎጂው የከርሰ ምድር የውሃ ሐብታችንን ሊያጎለብት የሚችል ነው፡፡
ፓርቲያችን ብልጽግና የዓለማችን የወደፊት የጉዞ አቅጣጫ ለሆነ ሌላ የቴክኖሎጂ መስክ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዚህ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፤ በዘርፉ የሰለጠነ ሰው ለማፍራም የተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርስቲዎች በዘርፉ ሥልጠና እየተሰጡ ነው፡፡
ይህ ዘርፍ ባለፉት አምስት ዓመታት (በተለይም ባለፉት 3 ዓመታት) በኢትዮጵያ ውስጥ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙት የቴክኖሎጂ ዘርፎች አንዱ ሲሆን ፓርቲያችን ብልጽግናም (ሮቦቲክስን ጨምሮ) አገራችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና ልማት ማዕከል እንድትሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህ ሴክተር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ዝቅተኛ ቢሆንም፤ ገዥው ፓርቲ እንደመንግስት በ87 ሚሊየን ዩሮ ያካሄደው የአይሲቲ መንደር ግንባታ፤ አገሪቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር የልቀት ማዕከል ለማድረግ ያለውን ትልቅ ህልም በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡ ሁለት የአገራችን ዩኒቨርስቲዎችም ራሳቸውን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ብቁ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ትብብር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የሮቦቲክስ የልቀት ማዕከልም ተቋቁሟል፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የሮቦቲክስ ዘርፍ ሥራን በማቀላጠፍ እና የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ፓርቲያችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል፤ ይህ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እንዲጠናከር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ ብቻ ሳይሆን የፓርቲያችንን ዲጂታል ኢኮኖሚ የመገንባት ግብ ተፈጻሚ ለማድረግ፤ ለቴሌኮም ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፤ ይህንም በመጪዎቹ ዓመታት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ብልጽግና የሚመራው መንግስት የኢትዮ ቴሌኮም የማቋቋሚያ ደንብ እንዲሻሻል እና ካፒታሉም ወደ 400 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ በማድረግ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት እንደሰጠ አረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የሚችልበትን መደላድል አመቻችቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም 137 የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የሲስተም አቅም ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ የኔትወርክ ሽፋን አቅምን እንዲሁም የአገልግሎት ጥራቱን ለማሳደግና ለማስፋፋት የሚያስችሉ ሰፋፊ ሥራዎችም በልዩ ትኩረት ተሰርተዋል፡፡
በቅርቡም፤ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የLTE Advanced Service አገልግሎት ተጀምሯል፡፡ በምስራቅ ሪጅን ጅጅጋ፣ ጎዴ፣ ዋርዴር፣ ፊቅ፣ ቀብሪደሃር፣ ቀብሪበያህ እና ደገሃቡር ከተሞች የLTE ሰርቪስ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም በደቡብ ሪጅን ያሉ እንደ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ቡታጅራ፣ ወልቂጤ፣ ጂንካና ሆሳዕና ያሉ ከተሞች የ4G LTE አገልግሎት በቅርቡ መጀመሩን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወረታ፣ ጎንደር፣ ቡሬ ወዘተ ባሉ ከተሞች የLTE Advanced Service አገልግሎት ተጀምሯል፡፡ ይህም ብልፅግና የያዘውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጥረት የሚያግዝ ይሆናል፡፡ ብልጽና የህን ሁሉ አቅዶ የሚፈጽመው ታላቋገር ኢትዮጵያ ብልጽና ይገባታል ብሎ ስለሚያምን ነው።
በመሆኑም ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትን እና የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጠውን፤ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርአት የመገንባት የ5 ዓመት ዕቅድ የነደፈውንና ኢትጵያን ከቀደመ ክብሯመመለስ የሚተጋውን ብልፅግናን ይምረጡ፡፡
እኛ ብልጽግና ነን!

ምላሽ ይስጡ