You are currently viewing ጥቂት ስለ ብልጽግና…

ጥቂት ስለ ብልጽግና…

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና በለውጡ ማግስት በይፋ ህዝብን ይቅርታ በመጠየቅ የጀመረው ጉዞ፤ ፖለቲካ ያለ ዜጎች ክብርና ልዕልና ትርጉም አልባ መሆኑን ያመላከተባቸውን በርካታ እርምጃዎች ወስዷል፡፡
በሺዎች ከእስር ሲፈቱ፤ በርካቶች ከስደት ተመልሰዋል፡፡ አዲስ በነደፈው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲው አማካኝነት በሰራው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አገራት እስር ላይ የነበሩ ዜጎች ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲኮሩ አድርጓል፡፡
ብልጽግና የሰራውም፣ እየሰራ ያለውም ሆነ ወደፊት የሚሰራው ዜጎች በያሉበት ቦታና አገር ክብራቸው ተጠብቆ፤ በማንነታቸው ሳይሸማቀቁ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ በማስቻል በሁለንተናዊ አገራዊ ብልፅግና ጉዞው ተሳታፊና የስኬቱም ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ነው፡፡
ስለዚህም በሁሉም ስፍራ ለሚገኙ ዜጎቻችን ክብርና ልዕልና በቁርጠኝነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት እየሰራ ያለውን ብልጽግና ይምረጡ፡፡

ምላሽ ይስጡ