You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ጥቂቶች መጠፋፋትን ሲሰብኩ አንድነት የታየን፤ መበታተንን ሲያስቡ መደመርን የተለምንና ያቀነቀንን፤  መጪው ዘመን ጨለማ ነው ሲሉን አይደለም የአገራችንን መጻዒ ዕድል ብርሃን ነው ስንል ያመላከትን፤ የዜጎችን ሃሳብ ተቀብለን ለአገር ጥቅም ያዋልን፤ ዴሞክራሲ እንዲያብብ መሰረቶችን ያስቀመጥን፤ የጥላቻ መሃንዲሶች ቂምና በቀልን ሲያስተምሩን በይቅርታ መሻገርን አጥብቀን የያዝንና ይህንንም በተግባር እያሳየን የመጣን ነን እኛ ብልጽግናዎች ነን፡፡

የችግሮች መፍቻ ሁሉ የጠብመንጃ አፈሙዝ ነው ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት ሰላማዊ መንገድን የመረጥን፤ የአብዮታዊ አስተሳሰብ በገነነበትና የጥላቻ ትርክቶች በነገሡበት ወቅት የህዝባችንን የልብ ትርታ አድምጠን የሰላም ሰንደቅ ያውለበልብንና ወንድማማችነትን ሰብከን የመጣን የለውጥ ኃይሎች ስብስብ የሆነውን ብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ የሀገራችንን ህልውና እናስቀጥል፡፡

ምላሽ ይስጡ