You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

የፖለቲካ ምርጫ ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት መሆኑ የሚረጋገጥበትና ለዚህም ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚያደርግበት አንዱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሂደት አካል ነው፡፡በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተዘጋጀላቸው እኩል መድረክ ተወዳድረው አማራጫቸውን ለህዝቡ በማቅረብ የመንግስት ስልጣን ውክልና የሚያገኙበት መንገድ ነው ምርጫ፡፡

ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ካለፉት አምስት የምርጫ ሂደቶች በእጅጉ የተለዬ ለማድረግ ማለትም ነጻ ማንም በማንም ሳይሸማቀቅ የፈለገውን መምረጥ የሚችልበት፣በመራጩ ህዝብ ዘንድ፣በምርጫ አስፈጻሚ አካላት፣በሀገር ውስጥና በውጭ ተጋባዥ ታዛቢዎች እንዲሁም በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ  ፍጹም ተዓማኒ ሆኖ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳዬ ይገኛል፡፡

በግንቦት ወር ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ እንደ ዜጋ ተሳታፊ ሆነው መወሰን እንዲችሉ የመራጭነት ካርድ ፈጥኖ ማውጣት ብልህነት ብቻም ሳይሆን ታሪካዊ ኃላፊነትም ተጥሎቦዎታል፡፡ሚሊዮኖች የሀገራቸውን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሚወስኑበት ዕለት ዴሞክራሲያዊ መብትዎን ለመጠቀም የመራጭነት ካርድ ዛሬውኑ ይውሰዱ፡፡

አምፖልን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ