You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

የጥላቻን ዘር ከስሩ በመንቀል፣ለጸብ መነሻ የሚሆኑ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማረም፣ወንድማማችነታችንን በማጠናከር እና ፍቅርን መስጠት፣የቆዬ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ማጠናከር፣ለሚገጥሙን እጅግ ፈታኝ  እና ውስብስብ ጋሬጣዎች ሳንደናገኝ ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሚና መጫወት ጊዜው የሚፈልገው ጉዳይ ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት ወንድማማችነት እና ሀገራዊ አንድነት ላይ ትኩረት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፤እየሰራም ይገኛል፡፡ጥላቻ ሀገርን አይደለም ግለሰብን እንኳ አይለውጥም፤የቆዩ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማራገብ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፤ጣት እየተቀሳሰሩ አንድነትን ማጠናከርም ሆነ በርካታ እና ውስብስብ የህዝብ ጥያቄዎችን መፍታት አይቻልም፡፡

ዛሬን በአግባቡ ተጠቅመን ሀገራችንን መገንባት የምንችለው እኔና እናንተ ነን፤የለማችና የበለጸገች ሀገርን በላባችን ፈጥረን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ካሻን ደግሞ ጫፍ ከወጣ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ ተላቆ ሀገርን ማስቀደም ያስፈልጋል፤መገፋፋት ሳይሆን መቀራረብን መምረጥ ይገባል፣እኔነትን ሳይሆን እኛነትን መልመድ የግድ ይላል፡፡ምክንያቱም ሀገር በግለሰቦች ብቻ አትገነባም በህዝቦች ንቁ ተሳትፎ እንጂ፣ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ለሀገር ዕድገት ሚና የላቸውም ማለት አይደለም፡፡

ሀገር የሁላችንም ድምር ውጤት ናት፡፡የሁላችንም ከሆነች ደግሞ ውድቀቷን ሳይሆን ከፍታዋን፣በጨለማ የተሸፈነች ሳይሆን በብርሃን የደመቀች ሀገር፣ሁከቷን ሳይሆን ሰላሟን ለትውልድ ለማስተላለፍ ነገን አስበን ዛሬን ከልብ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ህልም የመሰሉ በርካታ ድንቅ ስራዎች ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት ማስመዝገብ የቻለው ብልጽግና ፓርቲ ደግሞ ነገን አስቦ ዛሬ ላይ ህዝብን አስተባብሮ እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡

አምፖልን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ