You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ለአገርና ለሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ሲባል ኃላፊነትን በአግባቡ አለመጠቀመም ሆነ የሚፈጠሩ ችግሮችን በማባባስ ቀውስ መፍጠር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይጎዳል እንጂ አይጠቅማትም፡፡ ኢትዮጵያዊያንን በብሔርም ሆነ በሃይማኖት በማጋጨት ማጋደል፣ ማፈናቀልና ውድመት መፈጸም አዘቅት ውስጥ ይከታል እንጂ ዕድገት አያመጣም፡፡ ኢትዮጵያዊያን ወቅታዊ ችግሮችን ለመፍታት መነሳት አለባቸው፡፡
ከምንም ነገር በላይ ለአገራቸው ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል የማያንገራግሩት ኢትዮጵያዊያን በግልና በቡድን ጥቅም በሰከሩ ኃይሎች ግፍ ሲደርስባቸው ዝም መባል የለበትም፡፡
ሥልጣንን የመጨረሻ ግብ በማድረግ በሕዝብ ደም የሚነግዱ ኃይሎች አገር እንዲያተራምሱ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡ በተደጋጋሚ ሕዝብን ሰላም በመንሳትና ደኅንነቱን ለአደጋ በመዳረግ፣ ግላዊና ቡድናዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ወገኖችን ማስቆም ይገባል፡፡


አምፖልን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ