• Post comments:0 Comments

ሀገራችን ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ለማመን የሚከብዱ ግን ደግሞ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ የመጣበት ዓመታት ነበሩ ማለት ብዙዎችን የሚያስማማ ጉዳይ ነው፡፡በእርግጥም በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በውጭ ግንኙነት ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን ማምጣት ተችሏል፡፡
መንግስታዊ መዋቅሮችን ማሻሻል፣ለዓመታት በሚያራምዱት ፖለቲካዊ አቋማቸው ምክንያት እንደ ጠላት ተፈርጀው ከሀገር እንዲወጡ የተደረጉ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡ይህ የሚያሳየው የለውጡ አመራሮች ለሀገርና ለህዝብ ሰላም ያላቸውን የጸና አቋም ነው፡፡በማህበራዊና በውጭ ግንኙነት ዘርፍም የተመዘገቡ ውጤቶችን ማሳዬት ይቻላል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሶስት የለውጥ ዓመታት ለሀገራዊ አንድነትና ለህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት መጎልበት ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፤እየሰራም ይገኛል፡፡
በዚህም እንደ ሀገር ውጤት ማምጣት ተችሏል፤ምንም እንኳ ብልጽግና ፓርቲ ወንድማማችነት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ቢችልም ጥቅማቸው የተነካባቸው ሀይሎች ዛሬም እንደትናንቱ በህዝቡ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በመፈጸም የህዝብን ሰላም የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ይህን አሳዛኝና አሳፋሪ ክስተት ዳግም በኢትዮጵያ ምድር እንዳይመጣ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

አምፖልን ይምረጡ

Leave a Reply