You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ሰላም ስለተፈለገ ብቻ የሚገኝ ማህበራዊ ሀብት አይደለም፡፡እንዳያያዛችን ሁኔታ የሚወሰን እንጂ፡፡በአግባቡና በጥንቃቄ ከያዝነው ከእኛው አልፎ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን ከመግባባትና ነገሮችን በሰከነ መንገድ እንደ ሰለጠነ ዜጋ በውይይት መፍታት የማንችል ከሆነ ግን ሰላማችንን አጥተን በሰከንዶች ሽርፍራፊ ወደ ለየለት ግጭትና ትርምስ ውስጥ ሊያስገባን ይችላል፡፡ለዚህም ነው የሰላም ዋጋው ስንት ነው? የሚባለው፡፡


ሰላም ከየትም የሚመጣ ቁስ አይደለም፡፡ይልቁንም ከእኔ፣ ከእናንተ በአጠቃላይ ከሁላችንም መዳፍ የሚገኝ የሁላችንም እኩል ሀላፊነትን የሚፈልግ ልዩ ሀይል ያለው ማህበራዊ ሀብታችን ነው፡፡ እንደ ሀገር መልካም ስራዎችን ከማበረታታት ይልቅ ሰበቦችን እየፈለጉ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚፈልጉ እንቅፍ አጥተው የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ እሙን ነው፡፡


የህዝብና የሀገር ሰላም ማጣት ለማን በጄ? ችግሮች እንኳ ሲኖሩ ተቀራርበን ለችግሮቹ መፍትሔ ማምጣት ለመንግስት ወይም ለገዢው ፓርቲ ብቻ የሚተው ሳይሆን እያንዳንዳችን የመፍትሔው አንድ አካል እንደሆን ልናስብና የጋራ ሰላማችንን በተልካሻ ምክንያት እንዳናጣው ልንረባረብ ይገባል፡፡

ምላሽ ይስጡ