You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ስንደመር እንጠነክራለን“

ኢትዮጵያ የሁላችን ሀገር፤ የሁላችን ቤት ናት!

በአንድ ሀገር ውስጥ የሀሳብ ልዩነቶች ይኖራሉ። የሀሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም። ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ መደማመጥና በመርህ ላይ ተመስርተን መግባባት ስንችል የሀሳብ ልዩነት በረከት ይዞልን ይመጣል። በሀሳብ ፍጭት ውስጥ መፍትሄ ይገኛል። በመተባበር ውስጥ ኃይል አለ። ስንደመር እንጠነክራለን። አንድነት የማይፈታው ችግር አይኖርም… አገር ይገነባል።

የኔ ሀሳብ ካላሸነፈ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን እንኳን አገርን ሊያቆም ቤተሰብን ያፈርሳለ። ያለችን ኢትዮጵያ ነች ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት በላይ ሀገራዊ አንድነት ይበልጣል። አንድነት ማለት ግን አንድ ዓይነትነት ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል። አንድነታችን ልዩነቶቻችንን ያቀፈ ብዝሃነታችንን በህብረ-ብሔራዊነት ያደመደቀ መሆን አለበት።

”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዛሬ ሶስት ዓመት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸው ላይ ካደረጉት ንግግር ውስጥ የተወሰደ

ምላሽ ይስጡ