You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር የህግ የበላይነትን በማስከበር የሚገኘውን ሀገራዊ ትርፍ እና ከዚሁ ጎን ለጎን ሰላሟ የተጠበቀና በኢኮኖሚ ያደገች በሁለንተናዊ መልኩ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ብሎም ደህንነታቸው የተጠበቁ ዜጎች የሚንቀሳቀሱባት ሀገርን ለመፍጠር የህግ የበላይነት ማስከበርን አብይ አጀንዳው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ከዚህ የምንረዳው ብልጽግና ፓርቲ በህግ የበላይነት ላይ ምንም አይነት ድርድር እንደማያደርግ ነው፡፡


ህብረ ብሔራዊነትን ማጎልበት፣የወንድማማችነት እሴትን ማሳደግና መጠበቅ፣ዜጎች በዜግነታቸው ክብር የሚያገኙበት በማንነታቸው የማይሸማቀቁበት እንዲሁም በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ኢትዮጵያዊ ምድርን ለመፍጠር ከተፈለገ የግድ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡


ለዛም ነው ብልጽግና ፓርቲ ከውስጥም ከውጪም በሚገጥሙት ፈተናዎች እጅ ሳይሰጥ ህዝብን ማዕከል ያደረገ የህግ የበላይነት የማስከበር ስራውን እየሰራ ያለው፡፡
ብልጽግና እንደ ፓርቲ ሆኖ ማየት የሚፈልገው ጥቂቶች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት ስርዓትና ሀገር መፍጠር ሳይሆን የህግ የበላይነትን የተረዳና ለህግ ተገዢ የሆነ ማህበረሰብ ተገንብቶ ማየት ነው፡፡
አምፖልን ይምረጡ

ምላሽ ይስጡ