You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ ዘጠኝ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡በእነዚህ ዓመታት በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፎ እና በመንግስታችን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ውጤቶች ታጅቦ ዛሬ ላይ አፈፃፀሙ 79 ከመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡


ይህ ግድብ በኢትዮጵያዊያን አቅም እየተገነባ ያለ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክታችን ሲሆን ተጠናቆ የእንኳን ደስ አላችሁ ሪቫን እስኪቆረጥ ድረስ ሌት ተቀን በገንዘባችን በዕውቀታችንና በጉልበታችን የምናበረክተውን አስተዋፆኦ የምናሳድግ ይሆናል፡፡
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ተርፎን የምንገነባው የቅንጦት ፕሮጀክት ሳይሆን ከ60 ሚሊዬን የሚልቀው ህዛባችን ከጨለማ አውጥተን የብርሀን ፋኖስ እንዲያገኙ ለማስቻል የሚሰራ ግድብ ነው፡


በዚህም ሳያበቃ ለበርካታ ሺህ ዓመታት በወንዛችን መጠቀም ባለመቻላችን የተነሳ ዜጎቻችንን በረሃብ ውድ ህይወታቸው ሲያልፍ በቸነፈር ሲጠቁ ኑረዋል፡፡ አሁን ያን ሁሉ ሰቆቃ አልፈን በወንዛችን አልምተን መጠቀም እንደምንችል ለዓለም በተግባር ያሳየንበት እና እንደ ዓይን ብሌናችን ሌት ተቀን የምንመለከተውና የምንሳሳለት ግድባችን ነው፡፡ይህ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያበስረው ግድባችን በአፍሪካ በግዙፉነቱ ቀዳሚውን ቦታ ሲይዝ በዓለምም ካሉ ታላላቅ ግድቦች መካከል እስከ አስረኛ ደረጃ እንደሚይዝ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ፡፡


ግድቡን በራሳችን የውስጥ አቅም መስራታችን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ያስደመመው ከግድቡ ጋር በተያያዘ በርካታ መሰናክሎችን ታልፎ እያስመዘገብነው ያለው ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ አሁንም የግድባችንን ፍፃሜ እክል እንዲገጥመው እንቅልፍ አጥተው የሚሰሩ ከውስጥም ከውጪም ያሉ ባንዳዎችን ተቋቁመን በሀገር ጉዳይ ላይ የአንድነታችንን ከፍታ በማሳየት ለችግሮች እጅ የማንሰጥ ፅኑ ህዝብ መሆናችንን ግድባችንን አጠናቀን ማሳየት ይኖርብናል፤ለዚህ ደግሞ ብልጽግና ፓርቲ ሙሉ እይታውን ግድቡ ላይ በማድረግ ህዝብ የጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ምላሽ ይስጡ