You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ምርጫ በቂ የፖለቲካ ዕውቀት ያለውና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ መስጠት ወይም መምረጥ የሚችል ዜጋ የሚያስፈልገው ሒደት ነው፡፡ ይህ ዓይነት ዜጋ የሚፈጠረው በዋናነት በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ነው፡፡ ዜጎች ትክክለኛ ውሳኔና ምርጫ ማካሄድ እንዲችሉ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊነት በተሞላበትና የሙያ ሥነ ምግባሩን በጠበቀ ሁኔታ የፖለቲካ ተወዳዳሪዎችን ሙሉ ምሥል ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የሚዲያ ተቋማቱ ከምርጫ ጋር የተገናኙ ዜናዎችን ከማቅረብ ባለፈ፣ የክርክርና የውይይት መድረኮችን በመፍጠር ዜጎች የተለያዩ ሐሳቦችን ማንሸራሸር እንዲችሉ የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን አስመልክቶ በሚያስተላልፏቸው የሃሳብና የክርክር መድረኮች ከተሳሳተ ግንዛቤ እይታ እንዲወጡ የማስቻል ሃያል አውም አላቸው፡፡

በተለይ ደግሞ ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ተጠቅመው ይወክለኛል፣ይበጀኛል ያሉትንና ሀገራዊ እይታ ያለው፣ከልዩነት ይልቅ አንድነትን የሚያቀነቅን እንዲሁም አቃፊነትንና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ለመተግበር የሚተጋ ፓርቲን እንዲመርጡ መገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመስጠት በኩል የማይተካ ሚና አላቸው፡፡የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን የህዝብ ድምጽ እንዲከበርና ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ማስጨበጥ በተለዬ ሁኔታ በዚህ ወቅት ይጠበቃል፡፡

ድምጼን ለብልጽግና ፓርቲ እሰጣለሁ !

ምላሽ ይስጡ