You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ሰላሜን ስጡኝ እያለ ሌት ተቀን የሚማፀን ህዝብ፣የቀድሞው ወንድማማችነታችን ይበልጥብናል፣አብሮነታችን ይሻለናል ተውን ሰላሜን ስጡኝ ፣ሰላማችንን አታደፍርሱብን የብዙሀኑ ድምፅ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡
የሰላማችን መከበር የጀመርነውን የልማት፣ ዕድገትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የሚረዳን ይልቁንም የህዝቡን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ያለገደብና ያለፍርሀት መንቀሳቀስም ያስችለዋል እንጂ፡፡
የሀገራችንን ሠላም ጠብቀን ለማስጠበቅ ደግሞ የግድ ከመንግስት የተመደብን የፀጥታ ኃይል መጠበቅ አያስፈልግም ፤በዜግነታችን ብቻ ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡
የሀገራችን ሰላም የሁላችንም ሰላም መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ልዩ የወጣት አደረጃጀቶች፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዕምነት ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል።

Leave a Reply