You are currently viewing “ስላኮራችሁን፤ ከልብ እናመሰግናለን!!” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን

“ስላኮራችሁን፤ ከልብ እናመሰግናለን!!” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን

  • Post comments:0 Comments

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ላሳዩት ድጋፍና አጋርነት ተከታዩን ምስጋና አስተላልፈዋልእነሆ ዛሬ . . . በዋሽንግቶን ዲሲ ~ አሜሪካ የምትኖሩ ወገኖቻችን በጠንካራ የሃገር ፍቅር ስሜት፤ የኢትዮጵያን ትክክለኛ እና ወቅታዊ ገፅታ አስመልክቶ፤ ለሰፊው ዓለም እውነታውን ያስተጋባችሁበት ታሪካዊ ሰልፍ በእጅጉ የሚደነቅ ሲሆን ለፈፀማችሁት አኩሪ ተግባር ከልብ እናመሰግናለን፤ ደግሞም ኮርተንባችኋል።በተመሳሳይ በሌሎች ክፍለ ዓለማት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለውን ነባራዊ ዕውነት ለምዕራቡ ዓለም ለማስገንዘብ በታላቅ የንቅናቄ ሰልፍ ዝግጅት ላይ የምትገኙ ወገኖቻችንን ጨምሮ አስቀድሞ ታላቅ ምስጋና እና አክብሮታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ።በቀጣይ ሁላችንም እናት ሃገራችን ~ ኢትዮጵያን ከፊት አስቀድመን የፀና አንድነታችንን በማጥበቅ ወቅቱ ለሚጠይቀን ታሪካዊ ትግል በጋራ እንደምንረባረብ ከወዲሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።(ኢፕድ)

ምላሽ ይስጡ