• Post comments:0 Comments

ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶቻቸውን ጌጥ አድርገው በአንድነት ዘመናትን አብረው የኖሩት ለዘመናት የገነቧቸው የጋራ ማኅበራዊ እሴቶቻቸው የፈጠሩላቸው ቁርኝቶች በደም ስላስተሳሰሯቸው መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ከምንም ነገር በላይ ለአገራቸው ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል የማያንገራግሩት ኢትዮጵያዊያን ዛሬም እንደ ትናንቱ ዙሪያችንን የከበቡንን ፈተናዎች አሸንፈን ግባችን ወደሆነው ብልጽግና መገስገሳችን ዕሙን ነው፡፡  

የቆዬ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ማንም ሊሸረሽረው አይችልም፤ከፍ እያለ ይሄዳል እንጂ ከቶውንም ከከፍታው ሊወርድ አይችልም፡፡የአንድነታችን ጥንካሬ ለብዙዎች ትምህርት ሆኗል፡፡ከዛሬ 43 ዓመት በፊት የሶማሊያው የዚያድ ባሬ ጦር ኢትዮጵያን ሊወር በመጣ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ከምንም በላይ የሀገር ነጻነት ይቀድማል በሚል ወኔ ጦሩን መክተው ሃገሪቱን ከወራሪ የታደጉበት የካራማራ ድል ላሁኑ ትውልድ ከአድዋ ቀጥሎ ልንማርበት የሚገባ ገድል ነው።

ከምንም ከማንም በላይ ሥልጣንን የመጨረሻ ግብ በማድረግ እዛና እዚህ ሁከት ለመፍጠር ብሎም ሕዝብን ለማጋጨት የሚሹ ኃይሎች አደብ ሊገዙ ይገባል፤እንዲህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በመጣ ቁጥር በህዝብ ደም ለመነገድ እና የስልጣን ባለቤት እንሆናለን በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ቁማር ለመጫወት ፍላጎት ማሳዬት የተለመደ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡የሁላችንም ግብ ሊሆን የሚገባው ከድህነት ወጥተን ማደግን ነው፡፡

Leave a Reply