You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ለእኛ ኢትዮጵያውያን መነቃቃትን የፈጠረው እና በገሀድ እየታዬ ያለው ሀገራዊ ለውጥ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኩራት ሁኗቸው በየሚኖሩበት ሀገር በብሔርና በሀይማኖት ስንክሳር ውስጥ ታጥረው ከወንድማማችነት ይልቅ የጠላትነት ስሜት በውስጣቸው ሲብላላ ቢቆይም እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ በተግባር የታየው ሀገራዊ ለውጥ ግን ጥቁሩ መጋረጃ ተወግዶ ኢትዮጵያዊነት በልጆቿ በመላው ዓለም ከፍ ብሎ እንዲታይ አስችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት የጠንካራ አንድነት ጉልህ ፋይዳ ማሣያ መሆኑን ያመላክታል፡፡

ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት መጨመር፣ለፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት፣ለማህበራዊና አካባቢያዊ  እንቅስቃሴዎች መስፋፋት ወጣቱ ትውልድ ትልቅ ሚና እንዳለው የማይታበይ ሀቅ ነው።የሰላም መስፈን፣ የህግ የበላይነት መከበርና የዴሞክራሲ መጎልበት ለወጣቶች የሚኖራቸው ጠቀሜታ ቀላል አይደለም፤ በመሆኑም የሀገር ሰላም እንዳይደፈርስ፣ ብዝሃነትን ያከበረ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት እና ህብረ ብሔራዊነታችን ጎልብቶ በህዝቦቿ የደመቀች ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ ስንል ከውስጥም ሆነ ከውጭ ተላላኪ ሃይሎች ሊፈጸሙ የሚችሉ እኩይ ተግባራት በመመከት፣ በማጋለጥና በማክሸፍ የጀመርነውን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክረን በመቀጠል ሰላም ወዳድ ምክንያታዊ ትውልድ መሆናችንን በተግባር ልናሳይ ይገባናል፡፡

ደቡብ ኮሪያዊያን “እኛ የተወለድነው ለታሪካዊ ራዕይና ሀገራችንን ለመገንባት ነው” የሚል ዘመን ተሻጋሪና ከህሊና ሊጠፋ የማይችል ሀገረኛ አባባል አላቸው፡፡ በርግጥስ እነሱ እንደሚሉት ያለምክንያት የተፈጠረ ትውልድ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ?

ምላሽ ይስጡ