You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

ተግባብቶ ለአንድ አላማ ወይም ለጋራ ብልጽግና መስራት፣ ለሁሉን አቀፍ ለውጥ በጋራ መንቀሳቀስ፣ህብረ ብሔራዊነትን ሊያጎሉ የሚችሉ መተሳሰቦችን፣ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ ሊያቀራርቡን በሚችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መሰባሰብና መግባባት፣አንድነታችንን ለኢትዮጵያችን ህልውና መሰረት እንደሆነ አልመን መስራት ተገቢነት አለው፡፡

ሀገር የጋራችን ናት ስለሆነም በሀገር ጉዳይ ላይ እንደ ውጭ ዜጋ ከሩቅ ሆኖ ሃሳብ መሰንዘር ወይንም በምናገባኝ ስሜት ባይተዋር መሆን ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አያመላክትም፤እርግጥ ነው ብዙ የሚያስከፉን አሊያም ተስፋ የሚያስቆርጡን ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ወጣም ወረደም ግን ከሀገራችን ውጭ ሌላ ሀገር የለንም ፡፡ሀገራችን አንድ ናት እሷም ኢትዮጵያ፡፡ስለ ሀገራችን ሰላም፣ልማት፣ህብረ ብሔራዊነት መጎልበት፣የጎለበተ ዴሞክራሲ መፈጠር እንዲሁም ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማደግ የእያንዳንዳችን ድርሻ በእጅጉ የጎላ ነው፡፡

ሀገር ከድህነት ቀንበር ወጥታ ልማቷ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እስኪደርስ እና የዜጎች ተጠቃሚነት እስኪረጋገጥ ድረስ የምንተኛበት ምክንያት አይኖርም ፡፡ለሀገር ብልጽግና ከብልጽግና ሆኖ ሌት ተቀን መልፋትና መስራት ይጠይቃል፡፡

ምላሽ ይስጡ