ብልፅግና ፓርቲ ከራሺያው ዩናይትድ ራሺያ “United Russia” ፓርቲ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

ብልፅግና ፓርቲ ከራሺያው ዩናይትድ ራሺያ “United Russia” ፓርቲ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

  • Post comments:0 Comments

ብልፅግና ፓርቲ ከራሺያው ዩናይትድ ራሺያ “United Russia” ፓርቲ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በራሺያ መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ጥብቅ ወዳጅነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እና በፓርቲ ደረጃ ሊከወኑ የሚገባቸውን ጉዳዮች በጋራ ለመከወን የሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነው።

ይህም ሁለቱ ፓርቲዎች መርህ ላይ መሰረት ያደረገ ግንኙነትን እንዲያዳብሩ፣ከየትኛውም ጣልቃ ገብነት የፀዳ ግንኙነትን እንዲፈጥሩ ብሎም ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ዋና ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ሲሆኑ በሀገር ደረጃ ብልፅግና ፓርቲ እየሰራቸው ያሉ የለውጥ ስራዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ ለልኡካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።

በተለይም ነባራዊ ሁኔታዎችን ገምግሞ ብልፅግና ፓርቲ እየተከተለ የሚገኘው ሴንተሪዝም አይዲዮሎጂ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ዴሞክራሲ ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት እና ለዚህም መሳካት ከራሺያው ዩናይትድ ፓርቲ ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት ብልፅግና ፓርቲ እንዳለው ጠቅሰዋል።

ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲን ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት የፓርቲው የአለምአቀፍ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ የሆኑት ሚስተር አንድሬ ክሊሞቭ በበኩላቸው በርካታ ነጥቦችን ያነሱ ሲሆን ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመስራት ዝግጁነት እንዳለው ገልፀዋል። 

Leave a Reply