• Post comments:0 Comments

ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ እንደ ህዝብ ጥላቻ ኑሮበት አያውቅም ፡፡ነገር ግን በሁላችንም ውስጥ ያሉ ለሰላም ፀር የሆኑ፣ ሀሳባቸውን በህዝብ ስም ማስፈፀም የሚፈልጉ በርካቶች መኖራቸውን ግን መዘንጋት የለብንም፡፡

ለዚህም መፍትሄ እንዲሆን በጥቂቶች መነዳት፣በጥቂቶች መዘወር ሊበቃን ይገባል፡፡ብዙሀኑ ሰላም ወዳዱ ህዝብ ጥቂት እኩያንን እረፉ ሊል ይገባል፡፡ህዝብ እና የህዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ ያነጣጠረውን ይህን አካሄድ እንደ ሀገር ልናወግዘው ያስፈልጋል፡፡

ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍና ዝቅ ማለት፣ለዜጎች ስራ አጥነት ቁጥር ማደግ፣ቤታችን እና መተዳደሪያችን እተናደ ያለው ጥቂቶች እየደገሱ ባሉት የክፋት ድግስ ነውና ሁላችንም በማስተዋል ልንጓዝ ይገባል፡፡ ሰላም ወዳድነታችንን፤ አቃፊነታችንን፤ሰብአዊነታችንን ልንነጠቅ አይገባም፡፡

ሰላም ስንሆን ውበታችንና ሳቢነታችን ይጨምራል፤ አቃፊነታችን ሲያድግ ዓለም ላይ ተመራጭነታችን ያድጋል ፤ተመራጭነታችን ሲያድግም ሁላችንም በጋራ ማደግ መበልፀግ እንችላለን፡፡

Leave a Reply